spacer spacer Ethiopian Institution of the Ombudsman spacer spacer spacer
spacer spacer spacer spacer
spacer spacer spacer spacer
spacer spacer spacer spacer spacer spacer
shadow
English      
spacer shadow
spacer
spacer
ስለ እንባ ጠባቂ ተቋም

እንባ ጠባቂ አመጣጥ

በ The Free Encyclopaedia, (2006) መሰረት እንባ ጠባቂ (Ombudsman) የሚለው ቃል የተገኘው Umboosmaor ወይም Umbudsman, ከሚል ጾታን መሠረት ካላደረገ የጥንታዊ Norse ቃል ሲሆን ቃሉ ጠበቃ፣ ወኪል፣ ለውጥ አምጭ ከሚሉት ቃላት ጋር የሚዛመድ ትርጉም አለው፡፡

እንባ ጠባቂ ማለት ከፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ የሆነ የሕግ አውጪው አካል ተሿሚ ሲሆን እንባ ጠባቂው በሕግ እውቅና ያለው ግለሰብ (ተቋም) ነው፡፡ እንባ ጠባቂው uመንግስት ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል የደረሰባቸውን ዜጎች አቤቱታ በማዳመጥ ቅሬታዎቻቸውን መርምሮ መፍትሄ የሚያፈላልግ የሕዝብ አገልጋይ ነው ፡፡እንባ ጠባቂ ተቋም ለመጀመሪያ ጊዜ እአአ 1809 የተቋቋመ ሲሆን እንባጠባቂውም ፓርላሜንታዊ እንባ ጠባቂ በመባል ይታወቅ ነበር ፡፡

የኢፌዲሪ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ማቋቋም ለምን አስፈለገ

  • የኢፌዲሪ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 211/1992 መሰረት
  • ከህገ መንግስቱ ጋር የሚፃረሩ ህጎች መመሪያዎች እንዳይወጡ ለመከላከል፡
  • ግልጽነት ያለውና ቀልጣፋ የመንግስት አሰተዳደር እንዲኖር
  • ህግን በማክበር መሰረታዊ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ለማስፈን
  • በመንግስት አስፈፃሚ አካላት አድልዎ ያለመፈጸሙን ለማረጋገጥ
  • አስተዳደራዊ በደል እንዳይደርስ ለመከላከል፡፡

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዓላማ

የተቋሙ ዓላማ በህግ የተደነገጉ የዜጐች መብቶች እና ጥቅሞች በአስፈፃሚው አካላት መከበራቸውን በማረጋገጥ፣ የህግ የበላይነትን መሰረት ያደረገ ጥራት፣ ቅልጥፍናና ግልፅነት ያለው መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን ማድረግ ነው፡፡

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

  • አስፈፃፀሚ አካላት የሚያወጧቸው አስተዳደራዊ መመሪያዎች፣ የሚሰጧቸው ውሳኔዎችና አሰራሮቻቸው የዜጐችን ህገ-መንግስታዊ መብቶችና ህጐችን የማይቃረኑ መሆናቸውን መቆጣጠር፣
  • አስተደደራዊ ጥፋትን አስመልክቶ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን የመቀበልና የመመርመር፣
  • አስፈፃሚው አካል ስራውን በህግ መሰረት የሚያከናውን መሆኑን ለማረጋገጥና አስተዳደራዊ ጥፋቶች እዳይፈፀሙ ለመከላከል ቁጥጥር የማድረግ፣
  • አስተዳደራዊ ጥፋት መፈፀሙን ያመነበት ከሆነ የመፍትሄ ሀሳብ የመሻት፣
  • አስተዳደራዊ ጥፋቶች የሚሻሻሉበትን ሁኔታ የማጥናትና ሀሳብ የማቅረብ፣
  • የተሻለ የመንግስት አስተዳደርን ለማስገኘት ነባር ህጐች ወይም አሰራሮች ወይም መመሪያዎች እንዲሻሻሉ አዳዲስ ህጐች እንዲወጡ ወይም ፖሊሲዎች እንዲቀየሱ የማሳሰብ፣
  • ከዓላማው ጋር የሚጣጣሙ ሌሎች ተግባሮችን የማከናወን ስልጣንና ተግባራት አሉት፡፡
በአጠቃላይ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስተዳደራዊ ጥፋቶች እንዳይፈፀሙ መከላከልና ተፈፅመው ሲገኙም የሚታረሙበትን /የሚሻሻሉበትን/ የመፍትሄ ሀሳብ የማቅረብ ተግባራትን ያከናውናል፡፡


top

የኢፌዴሪ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የማያስተናግዳቸው ጉዳዮች

  • በማንኛውም ፍ/ቤት በየትኛውም ደረጃ በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮችን፣
  • በፌደራልም ሆነ በክልል ምክር ቤቶች የተላለፈ ውሳኔና በዋና ኦዲተር በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮችን፣
  • በፀጥታ ኃይሎችና በመከላከያ ሰራዊት ክፍሎች የሚሰጡ የፀጥታ ወይም የሀገር መከላከል ጉዳዮችን በሚመለከት የሚሰጡ ውሰኔዎችን፣
  • መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከሀይማኖት ተቋማት ከግለሰቦችና ከውጭ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አያይም፡፡

የተቋሙ ራዕይ

ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የመንግስት አስተዳደር የሰፈነባት ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያን ማየት፡፡

የተቋሙ ተልዕኮ

በመንግስት ተቋማት ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና አስተዳደራዊ በደልን ለመከላከል

ማስተማር፡- ህብረተሰቡ ስለመልካም አስተዳደር መርሆ¬ችና ስለ ህግ የበላይነት ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ ፣

ማበረታታት/ማገዝ፡- በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚፈጸም አስተዳደራዊ በደልን አስመልክቶ የሚቀርብ ቅሬታን ለመፍታት ተቋማቱ ስልት እንዲቀይር ማበረታታትና ማገዝ፣

መፍትሄ መሻት፡- አስተዳደራዊ በደልን አስመልክቶ የሚቀርብ ቅሬታን በአግባቡ በመቀበልና በመመርመር መፍትሔ መሻት፣

ማሻሻል፡- ጥናትና ምርምርን መሠረት በማድረግ አስተዳደራዊ በደል በሚታረምበት /በሚቀረፍበት/ ስልት ላይ ሀሳብ ማቅረብ፡፡

የተቋሙ ዕሴቶች፤

  • ገለልተኝነት፤
  • አለማዳላት፤
  • ዕኩልነትና ፍትሀዊነት፤
  • ቀልጣፋነትና ለህዝብ ቅርብ መሆን፣
  • ቅንነትና ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት፣
  • የፖሊሲና የኘሮግራሞች ግልፅነት፣
  • ምስጢር ጠባቂነት፤
  • ለህዝብ ተጠያቂ መሆን፤
  • በባለሙያና በቡድን ስራን መስራት፤
  • የህግ የበላይነትን ዲሞክራሲያዊ ሂደትንና መልካም አስተዳደርን ማክበርና ማስከበር ናቸው፡፡

top
spacer spacer

To properly view Amharic text, download and run this font installer.
Need help with Amharic typing?


ዜና እና ክንዋኔዎች
» ተጨማሪ

ምሳሌአዊ ዳውንሎዶች
» ተጨማሪ

የጎብኘወች አስተያየት
ይህን ድረ ገጵ የሚመለከቱ ሰዎች አስተያየታቸውን የሚሰጡበት መንገድ አዘጋጅተናል፡፡ እርሶም እስከ አሁን የተሰጡትን አስተያየቶች መመልከት ከፈለጉ እዚህ ጋር ይጫኑ

spacer
spacer
bottom